Thesis Open Access

የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ግምገማ፤ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በተዘጋጀው የ3ኛ ክፍል አማርኛ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ተተኳሪነት

በአብዮት አራጋው

Thesis supervisor(s)

በኢዮብ ቀለመወርቅ (ዶ/ር)

አጠቃሎ የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የ3ኛ ክፍል አማርኛ እንደ አፍመፍቻ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ግምገማ ነው፡፡ በመሆኑም የመማሪያ መጽሐፉ የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት በስፋትና በጥልቀት ተፈትሸዋል፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሳካት ወሳኝ የናሙና ዘዴ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ጥናቱም ዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልትን ተጠቅሟል፡፡ ጥናቱ በሰነድ ፍተሻ መረጃዎችን ሰብስቧል፡፡በሰነድ ፍተሻ የመረጃ መሰብሰቢያ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በዓይነታዊ ስልት በመጠቀም ተተንትኗል፡፡ ማብራሪያም ተደርጎባቸዋል፡፡ የጥናቱ ግኝትም በመማሪያ መጽሐፉ የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ካነሳቸው የይዘት አደረጃጀትና አቀራረብ አንጻር ተከታታይነትና ተለጣጣቂነት ጥሩ በሚባል አደረጃጀት እንደቀረቡ ተረጋግጣል፡፡ ዘጠና ሰባት በመቶ የሚሆነው የሰዋስው ይዘት ከአቀራረብ፣ ከተገቢት፣ ከግልጸኝነት፣ ከትክክለኛነት እና ከተመጣጣኝነት አንጻር እንደ ጠንካራ ጎን የታየ ሲሆን በመማሪያ መጽሐፉና ለደረጃው የተዘጋጀው መርሀ ትምህርት ግን በምዕራፍና በጊዜ አለመከፋፈሉ እንደ ድክመት ታይቷል፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግም በጥናቱ መጨረሻ ላይ ክፍተቱን ለመሙላት የሚያስችሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡

Files (707.2 kB)
Name Size
5. Abiyot Aragaw resrearch 1.pdf
md5:41f48e9f77604b7fc1074454fb8cb817
707.2 kB Download
0
0
views
downloads
All versions This version
Views 00
Downloads 00
Data volume 0 Bytes0 Bytes
Unique views 00
Unique downloads 00

Share

Cite as