Thesis Open Access

በ2004 ዓ.ም. በታተመው የዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ ያለው የሰዋስው ትምህርት ይዘት አደረጃጀት እና አቀራረብ ከመርሀ ትምህርቱ ጋር ያለው ተጣጥሞሽ

በእማዋዪሽ አርጋው

አጠቃሎ በዚህ ጥናት በ2004 ዓ.ም. በታተመው የ9ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሀፍ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጃት ከመርሀ ትምህርቱ ጋር ያለው ተጣጥሞሽ ምን እንደሚመስል ተገምግሟል፡፡ ጥናቱ አላማ አድርጎ በተነሳቸው ነጥቦች ዙሪያ የቋንቋ ምሁራን ያቀረቧቸውን ንድፈ ሀሳባዊ መሠረቶች መንደንደሪያ በማድረግ በሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ከመርሀ ትምህርቱ ጋር ያለው ተጣጥሞሽ ምን እንደሚመስል መነሳት ያለባቸውን ነጥቦች ተመልክቷል፡፡ ጥናቱን ከዳር ለማድረስ ጥቅም ላይ የዋለው የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ሰነድ ፍተሻ ሲሆን ይህም በአይነታዊ የምርምር ዘዴ መረጃው ተተንትኖ የተሰበሰቡት መረጃዎች በገላጭ ስልት ቀርቧል፡፡ በጥናቱ የተገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው በዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱት የሰዋሰው የይዘቶቹን አቀራረብ በተመለከተ ለክፍል ደረጃው ከተዘጋጀው መርሀ ትምህርት ጋር ተጣጣሚ እንደሆነ በሰነድ ፍተሻው ተረጋግጧል፡፡ በሌላ ክፍል መርሀ ትምህርቱ ከክህሎቱ አንጻር ከመማሪያ መጽሀፉ ጋር ተጣጥመው የቀረቡ እንዳልሆኑ ጥናቱ ያመላክታል ለዚህም የመፍትሄ ሀሳብ ተቀምጧል፡፡ ከአደረጃጀት አንጻርም መጽሀፉ አጠቃላይ በሆነው የይዘት አደረጃጀትና ከመርሃ ትምህርቱ ጋር ያለው ተጣጥሞሽ መልካም የሚባል ነው፡፡ በመጨረሻም በመማሪያ መጽሃፉ ውስጥ የተስተዋሉ መሻሻል ለሚገባቸው ሀሳቦች ይረዳሉ ተብለው የታመነባቸው የመፍትሄ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡

Files (727.8 kB)
Name Size
37. Emaway final tesis.pdf
md5:d673062ceb4a0c83df2af3dce164c3f0
727.8 kB Download
0
0
views
downloads
All versions This version
Views 00
Downloads 00
Data volume 0 Bytes0 Bytes
Unique views 00
Unique downloads 00

Share

Cite as